ይህ አራት ኮርስ የያዘ የጀማሪ ጥቅል ዲጂታል ቴክኖሎጂን ተጠቅመው እንዴት የእግዚአብሔርን ቃል ማሰራጨት እንደምትችሉ ያሳይዎታል። የአገልግሎቶን ተደራሽነት ለማሳደግ እና ሰዎቸን ለማነጽ ይዘጋጁ።

ይህ የጀማሪ ጥቅል የሚከተሉትን ኮርሶች ያካትታል


ኮርስ 1፡ ለምን ዲጂታል?


የበየነ መረብ አለምን የሚጠቀሙ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ከመምጣቱ አንጻር የዲጂታል ቴክኖሎጂን ሃይል ለወንጌል ስርጭት መጠቀም አስፈላጊ ነው። በዚህ ጥቅል ውስጥ ያለው የመግቢያ ኮርስ ዲጂታል ቴክኖሎጂ በአገልግሎት ውስጥ የሚጫወተውን ወሳኝ ሚና የሚያጎላ ሲሆን በዲጂታል መልክዓ ምድር ውስጥ ያሉ መመዘኛዎች፣ ተለዋዋጭነት እና የበየነ መረብ መሳሪያዎች ወንጌልን ይበልጥ ግልጽ በሆነ እና በተነጣጠረ መንገድ ለማስተላለፍ እንዴት እንደሚረዱ የሚያሳይ ነው።


ኮርስ 2፡ የፊልምን ኃይል ለወንጌል መጠቀም


በዚህ ጥቅል ውስጥ ያለው ሁለተኛው ኮርስ የቪዲዮን ሃይል እንዴት ወንጌልን ለማስፋፋት መጠቀም እንደምንችል ያሳየናል። ከስክሪፕት ጽሁፍ፤ ፕሮዳክሽን፤ ፖስት ፕሮዳክሽን እና ኤዲቲኝግ ድረስ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ቪዲዮዎችን በመፍጠር ሰዎችን እንዴት ማሳተፍ እና ማነቃቃት እንደሚችሉ ማወቅ ያለብዎትን ሁሉንም ነገር ይማራሉ ። በተጨማሪም ስለ ቅጂ እና ማከፋፈል በመማር የሚሰሩት ቪድዮ እንዴት በብዝ ሰዎች መታየት እንዲችል ማድረግ እንደሚችሉ ያውቃሉ።



ኮርስ 3፡ ፌስቡክ ማስታወቂያዎችን በመጠቀም የዲጂታል ወንጌል ስርጭት አሰራር


በዚህ ትቅል ውስጥ ያለው ሶስተኛ ኮርስ የፌስቡክ ማስታወቂያዎችን በመጠቀም የዲጂታል ወንጌል ስርጭት አሰራርን ያስተምሮታል። ትክክለኛ ሰዎችን የሚያነጣጥሩ ውጤታማ የፌስቡክ ማስታወቂያዎችን እንዴት መፍጠር እንደሚችሉ እና የበየነ መረብ ማህበረሰብዎን ለመገንባት ፌስቡክን እንዴት እንደሚጠቀም እንደሚችሉ ይማራሉ። እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2021 በአፍሪካ ብቻ የማይታመን 20ሺ መልዕክቶችን፣ 50ሺህ አስተያየቶችን እና 2 ሚሊዮን ቪዲዮ እይታዎችን ያመነጨውን የሲቪ በጣም ስኬታማ ዘመቻ/Ad የሆነውን "በእኩለ ለሊት" የተሰኘው ቪዲዮ እንዲት ፌስቡክ ላይ ያን ያህል ስኬት ማምጣት እንደቻለ ያያሉ።


ኮርስ 4፡ የበየነ መረብ ማህበረሰብ እንዴት መገንባት ይቻላል።


ባዚህ ጥቅል ያለው አራተኛው እና የመቸረሻው ኮርስ አገልግሎዎትን ጎል የሚደግፍ የዳበረ የበየነ መረብ ማሀበረሰብ ስለመገንባት ያስተምራል። የበየነ መረብ ማህበረሰብ ምን እንደሆነ፤ ይህ ማህበረሰብ ለአገልግሎቶዎ ያለው አስፈላጊነት፤ እንዲህም ይህን ማህበረሰብ እንዴት መገንባት፤ ማሳደግ እና መንከባከም እንደሚችሉ ይማራሉ። በተጨማሪም የበየነ መረብ ማህበረሰብዎን ስኬታማ ለማድረግ ትክክለኛ መሳሪያዎችን እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ እና የበየነ መረብ ማህበረሰቦች ሰነፍ ለሆኑ ሰዎች ብቻ ናቸው የሚለውን የተሳሳተ ግንዛቤ እንዴት ማሸነፍ እንደሚችሉ ይገነዘባሉ።