Online community image 2
የበየነ መረብ ማህበረሰብ የሚያበረክተው ተጽእኖ

“የተበተኑትም በየሄዱበት ሁሉ ቃሉን ሰበኩ" ሐዋሪያት ስራ 8፡4

 

ወንጌልን ለማካፈል በምናደርገው ጥረት የሐዋርያት ሥራ ምእራፍ 8 ቁጠር 4 ላይ የተጻፈውን መኖር እንፈልጋለን፣ ነገር ግን ስለ ኢየሱስ አብዝተው መስማት የሚያስፈልጋቸው ሰዎች በጉባኤያችን፣ በቤት ህብረቶች ወይም በአምልኮ ሥርዓቶች ውስጥ አይደሉም። አሁን ባለንበት የዲጂታል ዘመን፣ ሰዎች ባሉበት፤ በድህረ መረብ ላይ መገኘት አለብን።

በቅርብ ጊዜ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በአማካይ አንድ ሰው በይነመረብ ላይ የሚያሳልፈው ጊዜ በቀን ወደ 7 ሰዓታት ያህል ነው።


ስራ እና ማህበራዊ ግንኙነቶች በየነ መረብ ላይ ሲሆኑ, ሰዎች መገለል እና ብቸኝነት እንዲሰማቸው ሊያደርግ ይችላል፣ ይህም ከሌሎች ጋር የበለጠ ትርጉም ባለው መንገድ የመገናኘትን ፍላጎት እንዲጨምር ያደርጋል። የበየነ መረብ ማህበረሰቦች ሰዎች ሊኖሩበት የሚችሉበት ዲጂታል ቦታ በመሆን በሰዎች ህይወት ውስጥ ጉልህ ሚና ይጫወታል። አንድ ሰው ወደ ኦንላይን ለመሆን ስማርት ስልካቸውን ባነሳ ቁጥር በቀላሉ ከዲጂታል አገልግሎት ጋር ቢገናኝ ጥሩ አይሆንም! ይህ ኮርስ ይህንን እንዴት በትክክል ማድረግ እንደሚችሉ ያስተምርዎታል።

የተትረፈረፈ መከር


ከአለም ህዝብ ከግማሽ በላይ የሚሆነው በየነ መረብ ላይ ይገኛል፣ስለዚህ የራስዎን የበየነ መረብ ማህበረሰብ እንዴት መፍጠር እና መገንባት እንደሚችሉ በመማር ተደራሽነቶን ለማስፋት እድሉ እንዳያመልጥዎት። ዲጂታል አገልግሎት ከሰዎች ጋር ፊት ለፊት ያለውን መስተጋብር ሊተካ አይችልም፣ነገር ግን ወንጌልን ከአካላዊ አቅማችን በላይ የምናሰፋበት ኃይለኛ መንገድ ነው። የበየነ መረብ አገልግሎትህን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት እና አላማ ባለው መንገድ በመጠቀም ለተትረፈረፈ መከር ዘር መዝራት ይችላሉ።

Online community image 3
በዚህ ኮርስ የምናያቸው፡


የበየነ መረብ ህብራተሰብ ምን እንደሆነ

የበየነ መረብ ማህበረሰብ በአገልግሎትዎ ውስጥ ያለው ጠቀሜታ እና በአካል ለሚደረጉ አገልግሎቶች እንዴት ተጨማሪ ጠቀሜታ እንደሚሰጥ።

የበየነ መረብ ማህበረሰብ ለመመስርት ማድርገ ያለብዎት ነገሮች።

ማህበረሰቦን እንዴት ማሳድግ እንደሚችሉ።

ትክክለኛውን መሳሪያዎች እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ።

በመጨረሻም፤ የበየነ መረብ ማህበረሰብዎ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመምጣት የሰነፉ ሰዎችን ብቻ ያቀፈ ነው የሚለውን አስተሳሰብ ማሸነፍ።